ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ ለአካባቢው ህብረተሰብ የተለያዩ ድጋፍ የሚያደርግ እና ጉልህ ሚና የሚጫወት ድርጅት ነው፡፡ በተለይም የህብረተሰቡን ደህንነት የሚያስጠብቁ የድልድይ ፤ የውሃ ፍሳሽ ቱባ እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በተለይም ለመጭው ትውልድ በማሰብ ትህምህርት ቤቶችን በስፋት ይረዳል፡፡ በዚህም የትምህርት መማርያ ቁሳቁስ፤ የትምህርት ቤት ጥገና፤ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበሮችን እና መሰረት ቁሳቁሶችን ሲደግፍ ቆይቷል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ በተጠቃች ጊዜ ለሌሎች መስሪያ ቤቶች ሞዴል በሚሆን መልኩ ሁኔታዎችን በማጤን የሰው ሃብት አስተዳደር በሚመራው መልኩ ማናጅመንቱን በማሳተፍ ሊከናወኑ የሚገባቸውን ስራዎች ዕቅድ በማዘጋጀት እና የአፈጻጸም መርሃ ግብር በማዘጋጀት ሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንዲያደርስ የቅድመ ጥንቃቄ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ ሰራተኞ በቂ መረጃ እንዲያገኙ አስፈላጊውን የጥንቃቄ መልእክት ተላልፏል፡፡ የመከላከል ስራዎችን ለማከናወን ይረዳ ዘንድ ድርጅቱ አስፈላጊውን መርሃ ግብር ቀርጾ አገልግሎት ላይ አውሏል፡፡ በዚህም የሚከተሉት ስራዎች ተከናውነዋል
- የካንቲን አገልግሎትን የአካላዊ ርቀትን ባስጠበቀ መልኩ በሽፍት እንዲከናወን ተደርጓል
- የእጅ መታጠብያ ሳሙና እና ውሃ በሁሉም መግቢያና መውጫ በሮች፤ በስራ ቦታዎች እንዲዘጋጁ ተደርጓል፡፡ የሳኒታይዘር እና የፊት መሸፈኛ ማስክ እደላም ተከናውኗል
- በድርጅቱ ውስጥ የሚኒሚድያ አገልግሎ በክሊኒክ ባለሙያዎች በማስከፈት በሽታውን በተመለከተ ትክክለኛ መረጃዎች እንዲተላለፉ ተደርጓል
- ነባር የጤራ እክል ያለባቸውን ሰራተኞች በመለየት የአመት እረፍት እንዲወስዱ በማድረግ ሊደርስ የሚችለውን የጉዳት መጠን እንዲቀነስ ተደርጓል
- ለሰራተኞች ሰርቪስ አገልግሎ የሚሆኑ ተጨማሪ መኪናዎች ኪራይ ተከናውኗል
- የአካባቢው ህብረተሰብን በማሳተፍ የመከላከል ስራዎችን ሰርቷል
- ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከፍተኛ እንቅስቃሴ በሚደረግባቸው ቦታዎች ውሃ እና ሳሙና በማቅረብ በሽታውን የመከላከል ስራዎች ተሰርቷል
- የሰራተኛውን ሙቀት ለመለካት የሚውሉ የሙቀት መለኪያ መሳሪያ ከውጭ በማስመጣት አገልግሎት ላይ እንዲውል ተደርጓል
In practicing all the points mentioned above the company crafted COVID-19 prevention guideline and immediately started the operation.The green area plantation in and around our company is one of the environmental protection activity. The company is intensively working on the greening of the land found in the road side of the company dedicating financial and human resource. We transfer fair share of our profit for national and regional pandemic, economic crisis, stewardship arrangements and other contributions. In conclusion, we spend 27,029,257.63 birr in total for the above mentioned tasks between 2010 and 2015 budget year.