መረጃ
ያለንበት ዘመን በለውጥ የታጀበ እና ተለዋዋጭ ሲሆን ሆራይዘንድ አዲስ ጎማ አ.ማ ለውጡን በመቀላቀል የለውጡ አካል ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡ የጎማን ቴክኖሎጂን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ቀዳሚ ሲሆን በዚህም የውጭ ምንዛሬን በማዳን ለሃበሪቷ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህንንም ለማስፈጸም ብቃት ያላቸውን እና ቁርጠኛ ሰራተኞችን ቀጥሮ ያሰራል፡፡ ሆራይዘን አዲስ ጎማ ያለውን ራዕይ እና እሴቶች በሁሉም ሰራተኞች የተወረሰ ፤ የፈጠራ እና የቡድን ስራ የሚያበረታታ፤ ስኬት እና ውጤታማነትን የሚያጎለብት ድርጅት ነው፡፡ ሆራይዘን አዲስ ገማ ታማኝ፤ ግዙፍ ፤ የሚተማመኑበት ፤ ቀዳሚ እና የኢትዮጵያውያን ኩራት የሆነ ድርጅት ነው፡፡ እርስዎን ከላይ በተቀመጠው ውስጥ አግኝተዋል?