0

No products in the cart.

ጥሪ መቀበያ

+251114421555

በደንበኞች የሚጠየቁ ጥያዎች

በደንበኞች የሚጠየቁ ጥያዎች

ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ የማምቻ እና የማከፋፈያ ችርቻሮ ሱቅ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 401 ከሚቼል ኮትስ ፊት ለፊት ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የሽያጭ ሱቅ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ወረዳ 4 የቤት ቁጥር 1042/2 ከተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ይገኛል፡፡ ምርታችን በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች የሚገኝ ሲሆን በወኪል አከፋፋዮች በኩል በአዲስ አበባ፤ አዳማ፤ ሃዋሳ፤ ጂንካ፤ ሻሸመኔ፤ ወልቂጤ፤ወራቤ፤ ባህርዳር፤ ሞጣ ፤ ደብረማርቆስ፤ ደሴ፤ ጎንደር፤ ደብረብርሃን እና ወለጋ በስፋት ይገኛል፡፡

ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንት አምራች ኢንዱስትሪ ሲሆን ለተለያዩ ተሸከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች ማለትም የባለሦስት እግር ተሸከርካሪ ጎማ፣ የቀላል ተሸከርካሪዎች ባለክር ጎማ፣ የከባድ ተሸከርካሪዎች ባለክር ጎማ፣ የግሬደር ጎማ፣ የትራክተር ጎማ፣የፎርክ ሊፍት/ Industrial Bias/ ጎማ፣፤ የቀላል ተሸከርካሪዎች ባለሽቦ ጎማ /Light truck Radial (LTR)/ ፣ ፍሎቴሽን /FLOATATION/ ለስኳር ፋብሪካዎች ለሸንኮራ አገዳ ማመላለሻ የሚውሉ ጋሪዎች ጎማ እና ለመከላከያ ሰራዊት (Military Tire) ጎማዎችን፤ ፍላፕሶችን እና የጎማ ውጤቶችን አምርቶ ይሸጣል፡፡

ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪን እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር ከ 1972 ጀምሮ እያመረተ ይገኛል፡፡ 

የልህቀት ማዕረግ ተሸላሚ ከኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ከከፍተኛ አምራቾች ምድት የልህቀት ደረጃ ተሸላሚ ከአፍሪካ ካይዘን አዋርድ የላቀ ደረጃ የኢትዮጵያ ካይዘን ሽልማት ተሸላሚ ከኢትዮጵያ ካይዘን ሽልማት የብላደር አገልግሎት ዘመንን በማሳደግ 1ኛ ደረጃ የቡድን ተሸላሚ ከኢትዮጵያ ካይዘን ሽልማት የከባድ ነዳጅ አጠቃቀምን በመቀነስ 2ኛ ደረጃ የቡድን ተሸላሚ ከኢትዮጵያ ካይዘን ሽልማት የISO 9001-2015 ሰርተፍኬት ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት ISO 14001-2015 ሰርተፍኬት ከ ETA Umwelt management Ltd የወርቅ ደረጃ አውቶራይዝድ ኢኮኖሚክ ኦፕሬተር ሰርተፍኬት ከ ኢትዮጵያ ግምሩክ ባለስልጣን የዕውቅና የምስክር ወረቀት ከገቢዎች ሚኒስቴር የወረቅ ደረጃ ግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት ከገቢዎች ሚኒሰቴር

ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንት አምራች ኢንዱስትሪ ሲሆን ለተለያዩ ተሸከርካሪዎች እና ማሽነሪዎች ማለትም የባለሦስት እግር ተሸከርካሪ ጎማ፣ የቀላል ተሸከርካሪዎች ባለክር ጎማ፣ የከባድ ተሸከርካሪዎች ባለክር ጎማ፣ የግሬደር ጎማ፣ የትራክተር ጎማ፣የፎርክ ሊፍት/ Industrial Bias/ ጎማ፣፤ የቀላል ተሸከርካሪዎች ባለሽቦ ጎማ /Light truck Radial (LTR)/ ፣ ፍሎቴሽን /FLOATATION/ ለስኳር ፋብሪካዎች ለሸንኮራ አገዳ ማመላለሻ የሚውሉ ጋሪዎች ጎማ እና ለመከላከያ ሰራዊት (Military Tire) ጎማዎችን፤ ፍላፕሶችን እና የጎማ ውጤቶችን አምርቶ ይሸጣል፡፡

ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኑፋክቸሪንግ እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር በ2004 ለማታዶር በከፊል የተሸጠ ሲሆን ማታዶር 61 በመቶ የኢትዮጵያ መንግስት 31 በመቶ ሼር በመያዝ ሲተዳደር ቆይቷል፡፡ በ2011 ማታዶር ለኢትዮጵያዊው ድርጅት ለሆራይዘን ፕላንቴሽን ያለውን የ61 በመቶ ሼር በመሸጥ የባለቤትነት ድርሻውን አስተላልፏል፡፡ በመጨረሻም በ2013 ሆራይዘን ፕላንቴሽን ከኢትዮጵያ መንግስት ቀሪውን 31 በመቶ ሼር በመግዛት ሙሉ በሙሉ ድርጅቱን ማስተዳደር ችሏል፡፡

ድርጅቱ እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠበር በ1972 የጃፓንን የጎማ አመራረት ቴክኖሎጂን በመያዝ የተመሰረተ ሲሆን በጊዜውም በኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት አጼ ኃይለሥላሴ ተመርቆ ተከፍቷል፡፡ አዲስ ጎማ አ.ማ የጃፓኑን ዮኮሐማ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በ1964 ዓ.ም ስራ ሲጀምር የማምረት አቅሙ በዓመት 60,000 ጎማዎችና 45,000 የውስጥ ላስቲኮች ነበር፡፡ በግዜዉ ለ206 ለሚሆኑ ዘጎችም የስራ እድል ፈጥሯል፡፡

ለገጠሙት ጎማ አይነት ትክክለኛውን የአየር ሙሌት መጠን በጎማው ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ከድርጅታችን የምርት ካታሎግ ላይ፤ በድህረገጻችን ላይ፤ ከድርጅታችን ምርት ማከፋፈያ ሱቅ፤ ምርቶቻችንን ከሚያከፋፍሉ አከፋፋዮች፤ ሱቆች፤ ጎሚስታዎች ፤ ከድርጅቱ የጎማ መግጠሚያ ቦታ እና ከደንበኞ አገልግሎ ሰራተኞች ማግኘት ይችላሉ፡፡

  • ጎማ በትክክኛው አየር ሙሌት ሲሞላ ጎማው መሬቱን በጎማው የላይኛው ክፍል ወይም ትሬድ ሙሉ በሙሉ የሚቆነጥጥ ሲሆን ይህም ጎማው መሬትን በደንብ ቆንጥጦ በመያዝ እና ምቹ እና የተስተካከለ አነዳድን ያመጣል፡፡
  • ጎማን በትክክለኛ የሙሌት መጠን መሙላት የጎማውን የአገልግት ጊዜ ያራዝማል
  • ጎማ በተቀመጠው የሙሊት ምጣኔ መሙላት ተገቢ ነው

በዝቅተኛ መጠን ጎማ በአየር ሲሞላ የጎማው ትከሻ ብዙውን ክብደት የሚይዝ ሲሆን ይህም ክፍል በቶሎ እዲያልቅ ያደርጋል፡፡ የማህለኛው ክፍል ደግሞ ሳይበላ ይቀራል

በከፍተኛ መጠን ጎማ በአየር ሲሞላ የጎማው መሃለኛው ብዙውን ክብደት የሚይዝ ሲሆን ይህም ክፍል ቶሎ እንዲያልቅ ያደርጋል፡፡ የጎማው ትከሻ ደግሞ ሳይበላ ይቀራል፡፡

  • በተሳሳተ የጎማ አየር አሞላል ምክንያት ጎማው እኩል ባልሆነ መልኩ እንዲያልቅ ያደርጋል፡፡ በጎማ አገጣጠም ችግር ምክንያት በጎማው ቸርኬ አካባቢ ጉዳት ይደርሳል፡፡ በጎማ እና በመሪ አላይመንት ምክንያት ጎማ ያልሆነ ቅርጽ እንዲይዝ እና በትክክል እንዳያልቅ ያደርጋል፡፡ ፍሬን በተደጋጋሚ በሃይል በመያዝ ጎማ ያለአግባብ እንዲያልቅ ያደርጋል
  • እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የጎማ የአየር ሙሌትን በተቀመጠው መስፈርት መሰረት መሙላት፤ ጎማን ቸርኬ በማይጎዳ መልኩ የጎማ ማውጫ እና መግጠሙያ ማሽኖ ባሏቸው ጎሚስታዎች ብቻ ማስቀየር እና ማስጠገን፤ የመኪኖዎን የቴክኒካል አቋም ማስመርመር በተለይም የጎማ እና የመሪ አላይመንት እና እግር ጤንነት መከታተል

ጎማ አንድ በኩል የተበላ ከሆን የመኪናዎ እግር አካባቢ ችግር እንዳለ ይጠቁማል፡፡ ይህንንም አገልግሎት የሚያገኙበት ጋራዥ በመሄድ ማስመርመር ይኖርቦታል፡፡ በትክክለኛው የጎማ ሁኔታ መኪናው በሚነዳበት ወቅት በቀጥታ መስመር በትክክል ለመሄድ ያስችላል፡፡ ሆኖች በመኪናው እግር አካባቢ ችግሮች ሲኖሩ መሩ ወደ አንድ አቅጣጭ የሚያመዝን ይሆናል፡፡ መኪናውም ቀጥ ብሎ ለመሄድ አይችልም፡፡

  • ጎማ መገጠም ያለበት ልምድ ባላቸው እና የጎማ መግጠሚያ ማሽን ባላቸው ባለሙያዎች መሆን ይኖርበታል፡፡ በተለይም የራድያል ጎማ ከበገጠሙ በፊት ቸርኬው ንጹህ፤ ዝገት የሌለው፤ ያልተጎዳ፤ እብጠት ወይም ጉድጓዳ ቦታ የሌለው እና ያልተበየደ መሆኑ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ይህም የራዲያል ጎማዎች ከመነዳሪ የሌላቸው ስለሆነ ጎማው ምንም አይነት አየር እንዳያስወጣ በሚገጠሙበት ወቅት ጥንቃቄ ያስፈልጋቸዋል፡፡
  • ጎማ በሚገዙበት ወቅት ከፋብሪካ መሸጫ ሱቅ በመግዛት ድርጅቱ ባዘጋጀው የጎማ መግጠሚያ ቦታ ማስገጠም ይችላሉ፡፡ ሆኖም ጎማውን ከሌላ ቦታ ከዘዙ የጎማ መግጠሚያ እና መንቀያ ማሽን ያስገመጡ የተለያዩ ጎሚስታዎች በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ጎማውን ለመንቀልም ሆነ ለመግጠም የሚጠቀሙበት ማሽን ከማስገጠምዎ በፊት ጥሩ እንደሆነ ማየት እና ማረጋገጥ ይኖርብዎታል፡፡ በተለይም በሚገጠምበት ወቅት የቸርኬ መያዣ ወይም ቢድ አካባቢ ምንም እንዳይደበደብ እና ጉዳት እንዳይደርስበት መተታተል ያስፈላግል፡፡
amአማርኛ